Lyrics: Felix-Otto Jacoby/Feven Yoseph/Fritz Bayer/Jakob Hegner/Marcus Rust
Music: Felix-Otto Jacoby/Feven Yoseph/Fritz Bayer/Jakob Hegner/Marcus Rust
አየዋለሁ
ሲመሽ ከወንዙ ማዶ
ከጋራው ላይ ሆኜ
ህይወትን ሲሸምናት
በአልማዝ
በከዋክብት ስዬህ ሰማይ
ደጅ አድራለሁ አንተኑ ሳይ
ቦርከና ማዶ ከአቡኑ ግቢ ምሽት ሰማይ
የተባዘተ ጥጥ አለኝ ቋጨው ጊዜ ፈታይ
መቼ ልመስ መች ልምጣ ጊዜ ቁረጥልኝ
አልደርብበት አልቋጨው ውጥን ትዝታ አለኝ
እሰማዋለሁ
ስጓዝ በመንገዴ
ብቻዬን ሆኜ
ከቤቴ ሊያደርሰኝ
ጊዜ
በዝምታ እያወጋኝ
ከህይወት ምንጭ አደረሰኝ
ልቅዳ ልጠጣ ከምንጩ ትርካ በጄ ነፍሴ
ከዛፉ ጥላ አርፌ ልግባ ወደራሴ
ካመጣኝ ጊዜ መልሶ ወደ ልጅነቴ
ፈላ ወይ ልየው የጣልኩት ጠጅ አለ ከቤቴ
ቦርከና ማዶ ከአቡኑ ግቢ ምሽት ሰማይ
የተባዘተ ጥጥ አለኝ ቋጨው ጊዜ ፈታይ
መቼ ልመስ መች ልምጣ ጊዜ ቁረጥልኝ
አልደርብበት አልቋጨው ውጥን ትዝታ አለኝ
ልቅዳ ልጠጣ ከምንጩ ትርካ በጄ ነፍሴ
ከዛፉ ጥላ አርፌ ልግባ ወደራሴ
ካመጣኝ ጊዜ መልሶ ወደ ልጅነቴ
ፈላ ወይ ልየው የጣልኩት ጠጅ አለ ከቤቴ
አየዋለሁ አየዋለሁ
ሰማዋለሁ ሰማዋለሁ
ሂዎትን ሲሸምን አየዋለሁ
ሲያስዉባት በአልማዝ አየዋለሁ
አየዋለሁ አየዋለሁ
ሰማዋለሁ ሰማዋለሁ