Alat Liyu Gudai

Lyrics: Jonny Ragga/Nhatty Man This is a special collab you know Legendary Jonny Ragga alongside Nhatty Man
አይችሏትም በስታይል አይችሏትም በፋሽን አይችሏትም በስታይል አይችሏትም በፋሽን አላየሁ ሌላ ሴት ከሷ የምትሻል ሸልሟት ለድሏ የማራኪ ኒሻን
ከመድረሷ ገና ቦታው ድባቡ ይለወጣል ሁለመናዋ ውበት ታጥቆ ወጥታለች ምርኮ ለመጣል ከፀጉር እስከ ጥፍሯ ድረስ ቁንጅናዋ ፍጹም አይጣል ያያትም ላፍታ ወዶም ግኔታው ወዲያው እጅ ይሰጣል
አሎሎ ዓይኗ ሲንከባለል ተከትሎ የኔም ሊዋልል ችቦ ወገቧ እንደ እርጎ ይናጣል አካባቢውም አብሮ ይናወጣል
ጥርሷ በረዶ ነው ቤት ያደምቃል ፈገግታዋ ደምቆ ልብ ይሰርቃል ገና ሳያት ውበቷ አብሮ ሊመታ ልቤ እንደ ከበሮ
እሷ አላላላላላት እሷ አላት ልዩ ተልዕኮ ያደፈጠ ውበቷን ታኮ አፍዞ ለመጣል ምርኮ እሷ አላላላላላት ልጅቷ አላት ስውር ጉዳይ ዕምባው ነው ግብሩ የተበዳይ ልቡን ሰብራ የምትጥል ግዳይ
አይችሏትም በስታይል አይችሏትም በፋሽን አይችሏትም በስታይል አይችሏትም በፋሽን አላየሁ ሌላ ሴት ከሷ የምትሻል ሸልሟት ለድሏ የማራኪ ኒሻን
ለዛ ያለው ሲስቅ ሲጫወት ከብዙ አንድ ነው እንዲህ ያለ ውበት በመልኳ ወጥመድ ሁሉን አስጋሪ የወደዳትን እንባ አስገባሪ
ልጅቷ አመሏ ልዩ ነው ፀባይዋ ውበቷ ገዳይ ነው ገላዋ መለኛም ዘዴኛም ነች ጉብሏ የማትጠላ
ቀርቦም አይቶ አውግቷት አብሮ ውሎ ወላፈኗ ያልነካው ቢመስልም ችሎ ያልተረታ ማን አለ በሷ መውደድ በየተራ ተራ አንድ በአንድ
ፓ - ፓ - ታ- ታ ምላጭ ስባ ቃታ ገዳይ ነች ቀን ማታ አትሰጥም ፋታ ስንቱን ጣለችው ከእግሯ ስር የዋዛ አይደለም የሷስ ፍቅር ’
አይችሏትም በስታይል አይችሏትም በፋሽን አይችሏትም በስታይል አይችሏትም በፋሽን አላየሁ ሌላ ሴት ከሷ የምትሻል ሸልሟት ለድሏ የማራኪ ኒሻን
ሞሳድ ነች CIA ወይ ደሞ ኬጂቢ ስልጣኑን የሰጣት ይዛለች አጃቢ ጆኒ ራጋ ናቲ ማን ሚስጥሯን ዘጋቢ ብዙ ነው ታሪኳ ፋይሏ መቶ ጂቢ